*የቃላት አነባበብ (ጠ) ጠብቆ (ላ) ላልቶ
ድምጸ-ፖለቲካ
አፍ ካወራው/ ያነቡት(ጠ) ደንግሮ
ሲያሸበሽቡ/ ሌላ ተንደርድሮ፤
ለድምጸ-ፖለቲካ/ ቅላፄ ሞክሮ
የዜማውንም ጌታ፣ ቅዱስ ያሬድን/ ይጽፈው ቸግሮ።
ያዙ እንጂ
ለእግር ኳስ ጨዋታ/ ሕጉ እጅ አትንኩ
ለጥንጉ እንጂ/ ለሜዳው አትስጉ።
መሬቱ ቢደለደል/ ሣርም ብትፈልጉ
ነጫጮቹን መስመር/ ቀለም ብታደምቁ፤
ፊሽካ የሚነፋ/ ዳኛ የለም ጠንቁ።
Copyright © Yosef T Teklu. All rights reserved.
Lulu, Amazon, Barnes & Noble , and Book Depository
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.