*የቃላት አነባበብ (ጠ) ጠብቆ (ላ) ላልቶ
እማ
ወምበርማ ሄዶ/ መቼ ተቀመጠ?
ወምበር፡እማ(ጠ)/ ጌቶች አበለጠ!
ለምስኪኑ ዱካ/ እንጨት አልፈለጠ
መሬት እንጂ ጠርጎ/ እዛው የፈረጠ።
ወምበርማ - ምዕራብ ጎጃም ያለ መንደር
በየቤቱ
ምንጣፍ አነበቡ/ ጥንቆላ ከተረክ
የቆመበት እግር/ እርጥብ ወይም ደረቅ።
“ምን፡ጣፍ?” ጠየቁ/ ትንብይ ከተሰረግ
መጻኢው ዕድል/ መልካም ከተጠረግ።
Copyright © Yosef T Teklu. All rights reserved.
Lulu, Amazon, Barnes & Noble , and Book Depository