*የቃላት አነባበብ (ጠ) ጠብቆ (ላ) ላልቶ
ትዝብተ-ጦጣ
ቅጠል ጎዝጉዞ/ ና ጠርቶ
ዛፍ ሳለለት(ጠ)/ ቅርንጫፍ ዘርግቶ፤
ሰው ዕድለ-ቢሱ/ አመሉን ለውጦ
አቧራ በላ(ጠ)/ እመሬት ተቀምጦ።
እንጃ ምን እንደነካው/ ልጁን ደግሞ መልጦ፤
እጁ አጥሮ መጣ/ ከሄደበት ሮጦ
ጅራቱም ተቆርጦ።
ካልሆነ ታግዞ/ ያይ ብቻ አንጋጥጦ
መንጠልጠል ቸገረው/ እላይ ይውጣ ቀርቶ።
ቀልቤ(ጠ)
እንቁ ፈርጥዬ/ ራሪት ላንቺ ልቤ
አፈር እንዳይነካሽ/ “በሞቴ!” አስቤ።
ነፍሴን ሳዘለልሽው/ እንቁራሪት ቀልቤ(ላ)
ነይልኝ/ ወይ ልምጣ፣ ከካቤ ተስቤ
ቃል ኪዳን እገባሽ/ ካቧሯው ከንቤጠ።
ግና በዕድል ስባብ/ እባብ ተተብትቤ፤
ትጎመልይ እንደው/ አጣጠ-እጅ ቀርቤ
ጨው ባያሟሟው/ በአፌ ቀልቤ።
ቀልቤ - (ጠ) አብልቼ
-(ላ) ልቦናዬ፣ ሀሳቤ
- ይዤ
Copyright © Yosef T Teklu. All rights reserved.
Lulu, Amazon, Barnes & Noble , and Book Depository
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.