*የቃላት አነባበብ (ጠ) ጠብቆ (ላ) ላልቶ
አንተም?
አዳምን እሺ/ ሔዋን አሳስታ
መዘዝ ያበላችው/ ከዛ በለስ ቆርጣ።
አንድዬ አንተዬ/ ሐሳቤ ተምታታ
የበሰለ ልብኽ/ በማን እጅ ተረታ?
እኔ ሙሴ አማኝኽ/ ከበጎች ስመጣ
መንፈስኽ አርፎበት/ ፍሙም በቃቃታ፤
ነበልባል ባየሁኝ/ ጢሻ ዞሮ ቦታ
“ጌታም ተደበቀ?”/ አዝኛለሁ ፈንታ!
በል ተቀላቀለን/ ጨርቅ ያዝና በፍታ
ሽንጥኽ ታገልድመው/ ኀፍረትኽ እንዳይወጣ።
የኦሪት ዘጸአት ፫፥፪ ማናበቢያ
አብ አወራ
እየሱስ: ያጠገብዎትን አልፈው/ እርሶ ምነው ለእኔ?
አባወራ: እንዴ/ ምን አመጣው ቅኔ?
ውጪ አይቆሙ/ በጠራራው ሰኔ
ጥላ ላስገባዎት/ ከእልፍኝ ገመናዬ።
የልብ እውነታዬ
ካስቆጣዎት ውለታዬ፤
ይርሱት/ አብዬ ጌታዬ!
ልሂድ ልቀጥል/ ቤትና ዱካዬ
አቅን ከበደልኩት/ እመረምር፣ ሙያና ጠባዬ።
እርስዎ ደግሞ/ እኩያዬ
መገምገም ይያዙ/ ከጠሩት ሥራዬ፤
አሽሙር ተወሽቆ/ ታቅፎዎት በጉያዬ
እንዲኽ ያጠገብዎትን(ጠ)/ ሁሉ መከራዬ!
Copyright © Yosef T Teklu. All rights reserved.
Lulu, Amazon, Barnes & Noble , and Book Depository
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.